Mushaf Page 369
صفحة ٣٦٩
- Ghunnah
- Qalqalah
- Ikhfa (Haqiqi)
- Ikhfa Shafawi
- Idgham with Ghunnah
- Idgham without Ghunnah
- Idgham Shafawi (Mimi)
- Madd Lazim (6 counts)
- Madd Wajib Muttasil (4-5 counts)
- Madd Jaiz Munfasil (2, 4, 6 counts)
Each word’s meaning appears right below it; the transliteration follows below the words.
Surah ash-shuara
- لَعَلَّنَا نَتَّبِعُ السَّحَرَةَ إِن كَانُوا هُمُ الْغَالِبِينَ«ድግምተኞቹን እነሱ አሸናፊዎች ቢኾኑ እንከተል ዘንድ» (ተባለ)፡፡0 Views
- فَلَمَّا جَاءَ السَّحَرَةُ قَالُوا لِفِرْعَوْنَ أَئِنَّ لَنَا لَأَجْرًا إِن كُنَّا نَحْنُ الْغَالِبِينَ«ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ለፈርዖን እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለእኛ በእርግጥ ዋጋ አለን» አሉት፡፡0 Views
- قَالَ نَعَمْ وَإِنَّكُمْ إِذًا لَّمِنَ الْمُقَرَّبِينَ«አዎን፤ እናንተም ያን ጊዜ ከባለሟሎቹ ትኾናላችሁ» አላቸው፡፡0 Views
- قَالَ لَهُم مُّوسَىٰ أَلْقُوا مَا أَنتُم مُّلْقُونَሙሳ «ለእነርሱ እናንተ የምትጥሉትን ጣሉ» አላቸው፡፡0 Views
- فَأَلْقَوْا حِبَالَهُمْ وَعِصِيَّهُمْ وَقَالُوا بِعِزَّةِ فِرْعَوْنَ إِنَّا لَنَحْنُ الْغَالِبُونَገመዶቻቸውንና በትሮቻቸውንም ጣሉ፡፡ «በፈርዖንም ክብር ይኹንብን፡፡ እኛ በእርግጥ አሸናፊዎቹ እኛ ነን» አሉ፡፡0 Views
- فَأَلْقَىٰ مُوسَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ تَلْقَفُ مَا يَأْفِكُونَሙሳም በትሩን ጣለ፡፡ ወዲያውም እርሷ የሚያስመስሉትን ሁሉ ትውጣለች፡፡0 Views
- فَأُلْقِيَ السَّحَرَةُ سَاجِدِينَድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ፡፡0 Views
- قَالُوا آمَنَّا بِرَبِّ الْعَالَمِينَ(እነሱም) አሉ «በዓለማት ጌታ አመንን፡፡0 Views
- رَبِّ مُوسَىٰ وَهَارُونَ«በሙሳና በሃሩን ጌታ፡፡»0 Views
- قَالَ آمَنتُمْ لَهُ قَبْلَ أَنْ آذَنَ لَكُمْ ۖ إِنَّهُ لَكَبِيرُكُمُ الَّذِي عَلَّمَكُمُ السِّحْرَ فَلَسَوْفَ تَعْلَمُونَ ۚ لَأُقَطِّعَنَّ أَيْدِيَكُمْ وَأَرْجُلَكُم مِّنْ خِلَافٍ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمْ أَجْمَعِينَ(ፈርዖንም) «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን እርሱ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ታላቃችሁ ነው፡፡ ወደፊትም (የሚያገኛችሁን) በእርግጥ ታውቃላችሁ፡፡ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን (ቀኝና ግራን) በማናጋት እቆረርጣለሁ፡፡ ሁላችሁንም እሰቅላችኋለሁም» አለ፡፡0 Views
- قَالُوا لَا ضَيْرَ ۖ إِنَّا إِلَىٰ رَبِّنَا مُنقَلِبُونَ(እነርሱም) አሉ «ጉዳት የለብንም፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን፡፡0 Views
- إِنَّا نَطْمَعُ أَن يَغْفِرَ لَنَا رَبُّنَا خَطَايَانَا أَن كُنَّا أَوَّلَ الْمُؤْمِنِينَ«እኛ የምእምናን መጀመሪያ በመኾናችን ጌታችን ኀጢአቶቻችንን ለእኛ ሊምር እንከጅላለን፡፡»0 Views
- ۞ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ أَنْ أَسْرِ بِعِبَادِي إِنَّكُم مُّتَّبَعُونَወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ ሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና» ስንል ላክን፡፡0 Views
- فَأَرْسَلَ فِرْعَوْنُ فِي الْمَدَائِنِ حَاشِرِينَፈርዖንም በየከተሞቹ ሰብሳቢዎችን (እንዲህ ሲል) ላከ፡፡0 Views
- إِنَّ هَـٰؤُلَاءِ لَشِرْذِمَةٌ قَلِيلُونَ«እነዚህ ጥቂቶች ጭፈሮች ናቸው፡፡0 Views
- وَإِنَّهُمْ لَنَا لَغَائِظُونَ«እነርሱም ለእኛ አስቆጪዎች ናቸው፡፡0 Views
- وَإِنَّا لَجَمِيعٌ حَاذِرُونَ«እኛም ብዙዎች ጥንቁቆች ነን፤» (አለ)፡፡0 Views
- فَأَخْرَجْنَاهُم مِّن جَنَّاتٍ وَعُيُونٍአወጣናቸውም፡፡ ከአትክልቶችና ከምንጮች፡፡0 Views
- وَكُنُوزٍ وَمَقَامٍ كَرِيمٍከድልቦችም ከመልካም መቀመጫዎችም፡፡0 Views
- كَذَٰلِكَ وَأَوْرَثْنَاهَا بَنِي إِسْرَائِيلَእንደዚሁ ለእስራኤል ልጆች አወረስናትም፡፡0 Views
- فَأَتْبَعُوهُم مُّشْرِقِينَፀሐይዋ ስትወጣም ተከተሉዋቸው፡፡0 Views