70. al-maarij
المعارج
Read Surah al-maarij in full: surah 70, 44 verses, Meccan, Juz 29. Arabic text with አማርኛ translation.
- Ghunnah
- Qalqalah
- Ikhfa (Haqiqi)
- Ikhfa Shafawi
- Idgham with Ghunnah
- Idgham without Ghunnah
- Idgham Shafawi (Mimi)
- Madd Lazim (6 counts)
- Madd Wajib Muttasil (4-5 counts)
- Madd Jaiz Munfasil (2, 4, 6 counts)
Each word’s meaning appears right below it; the transliteration follows below the words.
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
- سَأَلَ سَائِلٌ بِعَذَابٍ وَاقِعٍወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡0 Views
- لِّلْكَافِرِينَ لَيْسَ لَهُ دَافِعٌበከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡0 Views
- مِّنَ اللَّهِ ذِي الْمَعَارِجِየ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡0 Views
- تَعْرُجُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍመላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡0 Views
- فَاصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًاመልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡0 Views
- إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيدًاእነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡0 Views
- وَنَرَاهُ قَرِيبًاእኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡0 Views
- يَوْمَ تَكُونُ السَّمَاءُ كَالْمُهْلِሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡0 Views
- وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡0 Views
- وَلَا يَسْأَلُ حَمِيمٌ حَمِيمًاዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡0 Views
- يُبَصَّرُونَهُمْ ۚ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ(ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡0 Views
- وَصَاحِبَتِهِ وَأَخِيهِበሚስቱም በወንድሙም፡፡0 Views
- وَفَصِيلَتِهِ الَّتِي تُؤْوِيهِበዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡0 Views
- وَمَن فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ يُنجِيهِበምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡0 Views
- كَلَّا ۖ إِنَّهَا لَظَىٰይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡0 Views
- نَزَّاعَةً لِّلشَّوَىٰየራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡0 Views
- تَدْعُو مَنْ أَدْبَرَ وَتَوَلَّىٰ(ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡0 Views
- وَجَمَعَ فَأَوْعَىٰገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡0 Views
- ۞ إِنَّ الْإِنسَانَ خُلِقَ هَلُوعًاሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡0 Views
- إِذَا مَسَّهُ الشَّرُّ جَزُوعًاክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡0 Views
- وَإِذَا مَسَّهُ الْخَيْرُ مَنُوعًاመልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡0 Views
- إِلَّا الْمُصَلِّينَሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡0 Views
- الَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ دَائِمُونَእነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡0 Views
- وَالَّذِينَ فِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ مَّعْلُومٌእነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡0 Views
- لِّلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡0 Views
- وَالَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوْمِ الدِّينِእነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡0 Views
- وَالَّذِينَ هُم مِّنْ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشْفِقُونَእነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡0 Views
- إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمْ غَيْرُ مَأْمُونٍየጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡0 Views
- وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَእነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡0 Views
- إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَበሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡0 Views
- فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡0 Views
- وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَእነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡0 Views
- وَالَّذِينَ هُم بِشَهَادَاتِهِمْ قَائِمُونَእነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡0 Views
- وَالَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ يُحَافِظُونَእነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡0 Views
- أُولَـٰئِكَ فِي جَنَّاتٍ مُّكْرَمُونَእነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡0 Views
- فَمَالِ الَّذِينَ كَفَرُوا قِبَلَكَ مُهْطِعِينَለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?0 Views
- عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ عِزِينَከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡0 Views
- أَيَطْمَعُ كُلُّ امْرِئٍ مِّنْهُمْ أَن يُدْخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٍከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?0 Views
- كَلَّا ۖ إِنَّا خَلَقْنَاهُم مِّمَّا يَعْلَمُونَይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡0 Views
- فَلَا أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَበምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡0 Views
- عَلَىٰ أَن نُّبَدِّلَ خَيْرًا مِّنْهُمْ وَمَا نَحْنُ بِمَسْبُوقِينَከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡0 Views
- فَذَرْهُمْ يَخُوضُوا وَيَلْعَبُوا حَتَّىٰ يُلَاقُوا يَوْمَهُمُ الَّذِي يُوعَدُونَያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡0 Views
- يَوْمَ يَخْرُجُونَ مِنَ الْأَجْدَاثِ سِرَاعًا كَأَنَّهُمْ إِلَىٰ نُصُبٍ يُوفِضُونَወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡0 Views
- خَاشِعَةً أَبْصَارُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ ۚ ذَٰلِكَ الْيَوْمُ الَّذِي كَانُوا يُوعَدُونَዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡0 Views
Teks Al-Qur'an: Tanzil Project (https://tanzil.net), lisensi CC BY 3.0. · Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib (Tanzil Project, tanzil.net)