68. al-qalam
القلم
Read Surah al-qalam in full: surah 68, 52 verses, Meccan, Juz 29. Arabic text with አማርኛ translation.
- Ghunnah
- Qalqalah
- Ikhfa (Haqiqi)
- Ikhfa Shafawi
- Idgham with Ghunnah
- Idgham without Ghunnah
- Idgham Shafawi (Mimi)
- Madd Lazim (6 counts)
- Madd Wajib Muttasil (4-5 counts)
- Madd Jaiz Munfasil (2, 4, 6 counts)
Each word’s meaning appears right below it; the transliteration follows below the words.
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
- نٓ ۚ وَالْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَነ.(ኑን)፤ በብርእ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት፡፡0 Views
- مَا أَنتَ بِنِعْمَةِ رَبِّكَ بِمَجْنُونٍአንተ በጌታህ ጸጋ የተጎናጸፍክ ስትኾን ዕብድ አይደለህም፡፡0 Views
- وَإِنَّ لَكَ لَأَجْرًا غَيْرَ مَمْنُونٍላንተም (ከጌታህ) የማይቋረጥ ዋጋ በእርግጥ አልለህ፡፡0 Views
- وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍአንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ፡፡0 Views
- فَسَتُبْصِرُ وَيُبْصِرُونَወደፊትም ታያለህ፤ ያያሉም፡፡0 Views
- بِأَييِّكُمُ الْمَفْتُونُዕብደት በማንኛችሁ እንዳልለ፡፡0 Views
- إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِ وَهُوَ أَعْلَمُ بِالْمُهْتَدِينَጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ተመሪዎቹን ዐዋቂ ነው፡፡0 Views
- فَلَا تُطِعِ الْمُكَذِّبِينَለአስተባባዮችም አትታዝዙ፡፡0 Views
- وَدُّوا لَوْ تُدْهِنُ فَيُدْهِنُونَብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡0 Views
- وَلَا تُطِعْ كُلَّ حَلَّافٍ مَّهِينٍወራዳንም ሁሉ አትታዘዝ፡፡0 Views
- هَمَّازٍ مَّشَّاءٍ بِنَمِيمٍሰውን አነዋሪንና በማሳበቅ ኼያጅን፡፡0 Views
- مَّنَّاعٍ لِّلْخَيْرِ مُعْتَدٍ أَثِيمٍለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፣ ወሰን አላፊን፣ ኃጢአተኛን፤0 Views
- عُتُلٍّ بَعْدَ ذَٰلِكَ زَنِيمٍልበ ደረቅን፣ ከዚህ በኋላ ዲቃላን (ሁሉ አትታዘዝ)፡፡0 Views
- أَن كَانَ ذَا مَالٍ وَبَنِينَየገንዘብና የልጆች ባለቤት በመኾኑ (ያስተባብላል)፡፡0 Views
- إِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِ آيَاتُنَا قَالَ أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَበእርሱ ላይ አንቀጾቻችን በሚነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡0 Views
- سَنَسِمُهُ عَلَى الْخُرْطُومِበአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክት እናደርግበታለን፡፡0 Views
- إِنَّا بَلَوْنَاهُمْ كَمَا بَلَوْنَا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ إِذْ أَقْسَمُوا لَيَصْرِمُنَّهَا مُصْبِحِينَእኛ የአትክልቲቱን ባለቤቶቸ እንደ ሞከርን (የመካን ሰዎች) ሞከርናቸው፡፡ ማልደው (ፍሬዋን) ሊለቅሟት በማሉ ጊዜ፡፡0 Views
- وَلَا يَسْتَثْنُونَ(በመሓላቸው) አያስቀሩምም፡፡0 Views
- فَطَافَ عَلَيْهَا طَائِفٌ مِّن رَّبِّكَ وَهُمْ نَائِمُونَእነርሱ የተኙ ኾነውም ሳሉ ከጌታህ የኾነ ዟሪ በእርሷ ላይ ዞረባት፡፡0 Views
- فَأَصْبَحَتْ كَالصَّرِيمِእንደ ሌሊት ጨለማም ኾና አነጋች፤ (ከሰለች)፡፡0 Views
- فَتَنَادَوْا مُصْبِحِينَያነጉም ኾነው ተጠራሩ፡፡0 Views
- أَنِ اغْدُوا عَلَىٰ حَرْثِكُمْ إِن كُنتُمْ صَارِمِينَ«ቆራጮች እንደ ኾናችሁ በእርሻቸሁ ላይ ማልዱ» በማለት፡፡0 Views
- فَانطَلَقُوا وَهُمْ يَتَخَافَتُونَእነርሱ የሚንሾካሾኩ ኾነው ኼዱም፡፡0 Views
- أَن لَّا يَدْخُلَنَّهَا الْيَوْمَ عَلَيْكُم مِّسْكِينٌዛሬ በእናንተ ላይ ድኻ እንዳይገባት በማለት፡፡0 Views
- وَغَدَوْا عَلَىٰ حَرْدٍ قَادِرِينَ(ድኾችን) በመከልከልም ላይ (በሐሳባቸው) ቻዮች ኾነው ማለዱ፡፡0 Views
- فَلَمَّا رَأَوْهَا قَالُوا إِنَّا لَضَالُّونَ(ተቃጥላ) ባዩዋትም ጊዜ «እኛ በእርግጥ ተሳሳቾች ነን» አሉ፡፡0 Views
- بَلْ نَحْنُ مَحْرُومُونَ«ይልቁንም እኛ የተከለከልን ነን» አሉ፡፡0 Views
- قَالَ أَوْسَطُهُمْ أَلَمْ أَقُل لَّكُمْ لَوْلَا تُسَبِّحُونَትክክለኛቸው «ለእናንተ አላህን ለምን አታጠሩም አላልኳችሁምን?» አላቸው፡፡0 Views
- قَالُوا سُبْحَانَ رَبِّنَا إِنَّا كُنَّا ظَالِمِينَ«ጌታችን ጥራት ይገባው፡፡ እኛ በዳዮች ነበርን፤» አሉ፡፡0 Views
- فَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ يَتَلَاوَمُونَየሚወቃቀሱም ኾነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ፡፡0 Views
- قَالُوا يَا وَيْلَنَا إِنَّا كُنَّا طَاغِينَ«ዋ ጥፋታችን! እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን፤» አሉ፡፡0 Views
- عَسَىٰ رَبُّنَا أَن يُبْدِلَنَا خَيْرًا مِّنْهَا إِنَّا إِلَىٰ رَبِّنَا رَاغِبُونَ«ጌታችን ከእርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጀላል፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ከጃዮች ነን፤» (አሉ)፡፡0 Views
- كَذَٰلِكَ الْعَذَابُ ۖ وَلَعَذَابُ الْآخِرَةِ أَكْبَرُ ۚ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَቅጣቱ እንደዚሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ታላቅ ነው፡፡ የሚያውቁት በኾኑ ኖሮ (በተጠነቀቁ ነበር)፡፡0 Views
- إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتِ النَّعِيمِለጥንቁቆቹ በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው፡፡0 Views
- أَفَنَجْعَلُ الْمُسْلِمِينَ كَالْمُجْرِمِينَሙስሊሞቹን እንደ ከሓዲዎች እናደርጋለን?0 Views
- مَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ፡፡0 Views
- أَمْ لَكُمْ كِتَابٌ فِيهِ تَدْرُسُونَበእውነቱ ለእናንተ በእርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን?0 Views
- إِنَّ لَكُمْ فِيهِ لَمَا تَخَيَّرُونَበውስጡ ለእናንተ የምትመርጡት አላችሁ (የሚል)0 Views
- أَمْ لَكُمْ أَيْمَانٌ عَلَيْنَا بَالِغَةٌ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ ۙ إِنَّ لَكُمْ لَمَا تَحْكُمُونَወይስ ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሣኤ ቀን ደራሽ የኾኑ መሓላዎች ለእናንተ በእኛ ላይ አሏችሁን?0 Views
- سَلْهُمْ أَيُّهُم بِذَٰلِكَ زَعِيمٌበዚህ ማንኛቸው ተያያዥ እንደ ኾነ ጠይቃቸው፡፡0 Views
- أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ فَلْيَأْتُوا بِشُرَكَائِهِمْ إِن كَانُوا صَادِقِينَወይስ ለእነርሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) «ተጋሪዎች» አሏቸውን? እውነተኞችም እንደኾኑ «ተጋሪዎቻቸውን» ያምጡ፡፡0 Views
- يَوْمَ يُكْشَفُ عَن سَاقٍ وَيُدْعَوْنَ إِلَى السُّجُودِ فَلَا يَسْتَطِيعُونَባት የሚገለጥበትን (ከሓዲዎች) ወደ መስገድም የሚጥጠሩበትንና የማይችሉበት ቀን (አስታውስ)፡፡0 Views
- خَاشِعَةً أَبْصَارُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ ۖ وَقَدْ كَانُوا يُدْعَوْنَ إِلَى السُّجُودِ وَهُمْ سَالِمُونَዓይኖቻቸው የፈሩ ውርደት የምትሸፍናቸው ሲኾኑ፤ (ወደ ስግደት የሚጠሩበትን)፤ እነርሱም (በምድረ ዓለም) ደህና ኾነው ሳሉ ወደ ስግደት በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ፡፡0 Views
- فَذَرْنِي وَمَن يُكَذِّبُ بِهَـٰذَا الْحَدِيثِ ۖ سَنَسْتَدْرِجُهُم مِّنْ حَيْثُ لَا يَعْلَمُونَበዚህም ንግግር ከሚያስተባብሉት ሰዎች ጋር ተዎኝ፡፡ (እነርሱን እኔ እበቃሃለሁ)፡፡ ከማያውቁት ስፍራ አዘናግተን እንይዛቸዋለን፡፡0 Views
- وَأُمْلِي لَهُمْ ۚ إِنَّ كَيْدِي مَتِينٌእነርሱንም አዘገያለሁ፡፡ ዘዴዬ ብርቱ ነውና፡፡0 Views
- أَمْ تَسْأَلُهُمْ أَجْرًا فَهُم مِّن مَّغْرَمٍ مُّثْقَلُونَበእውነቱ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳ የተከበዱ ናቸውን?0 Views
- أَمْ عِندَهُمُ الْغَيْبُ فَهُمْ يَكْتُبُونَወይስ እነርሱ ዘንድ የሩቁ ምስጢር ዕውቀት አልለን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን?0 Views
- فَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلَا تَكُن كَصَاحِبِ الْحُوتِ إِذْ نَادَىٰ وَهُوَ مَكْظُومٌለጌታህም ፍርድ ታገሥ፤ (በመበሳጨትና ባለ መታገሥ) እንደ ዓሣው ባለቤትም (እንደ ዮናስ) አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ (ጌታውን) በተጣራ ጊዜ፡፡3 Views
- لَّوْلَا أَن تَدَارَكَهُ نِعْمَةٌ مِّن رَّبِّهِ لَنُبِذَ بِالْعَرَاءِ وَهُوَ مَذْمُومٌከጌታው የኾነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በምድረ በዳ ተወቃሽ ኾኖ በተጣለ ነበር፡፡3 Views
- فَاجْتَبَاهُ رَبُّهُ فَجَعَلَهُ مِنَ الصَّالِحِينَጌታውም (በነቢይነት) መረጠው፡፡ ከደጋጎቹም አደረገው፡፡3 Views
- وَإِن يَكَادُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَيُزْلِقُونَكَ بِأَبْصَارِهِمْ لَمَّا سَمِعُوا الذِّكْرَ وَيَقُولُونَ إِنَّهُ لَمَجْنُونٌእነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቀርባሉ፡፡ «እርሱም በእርግጥ ዕብድ ነው» ይላሉ፡፡3 Views
- وَمَا هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِّلْعَالَمِينَግን እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡3 Views
Teks Al-Qur'an: Tanzil Project (https://tanzil.net), lisensi CC BY 3.0. · Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib (Tanzil Project, tanzil.net)